የዳኞች ስልጠና ምዘና ቡድን መሪ

የዳኞች ስልጠና ምዘና ቡድን መሪ

  • ከዲይሬክቶሬቱ ስትራቴጅክ እቅድ በመነሳት የቡድኑን ዕቅድ ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
  • የቡድን እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ከባለሙያዎች ጋር በመሆን በጋራ ይገመግማል፣ለዲይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
  • አመታዊ የዳኞች የዳኝነት ስራ አፈጻጸም ምዘና እቅድ ማዘጋጀት፣ ምዘና ነጥቦችን ስታንዳርድ ከዳይሬክተሩ ጋር በጋራ ማዘጋጀት፣ምዘና ከባለሞያ ጋር በመሆን ማካሄድ፣ የምዘና ውጤትን አደራጅቶ በዳይሬክቶሬቱ ማቅረብ፣
  • በዳኞች ምዘና የተለዩ የህግ አተረጓጎም ክፍተቶችን፣ የአሰራር ክፍተቶችን ፣ሌሎች የስነ-ምግባር ክፍተቶች እንዲለዩ በማድረግ በዳይሬክተሩ ማቅረብ፤
  • በዳኞችን የዳኝነት አገልግሎት አፈጻጸም ላይ ጥናቶችን በማድረግ የስልጠና ፍላጎትን መለየት ለዳይሬክተሩ ማሳወቅ፤
  • ስልጠናዎችን ማቀድ ፣ የስልጠና በጀት ማቀድ፣እንዲፈጸሙም ማድረግ፣ የአፈጻጸማቸውን ውጤትም ሪፖርት በዲይሬክተሩ ማቅረብ፣