ዘርፎች

አዲስ አበባ ከተማ ይግብኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

image description

አቶ ታደሰ ፈይሳ አሰፋ

የፕሬዝዳንት የጽ/ቤት ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት የጽ/ቤት ኃላፊው ተጠሪነቱ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ ሆኖ የሚከተለት ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡ ለተቋሙ ኃላፊ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎችን በሚሰጠው ውክልና መሠረት ያስተባብራል፣ ወቅታዊ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ያደርጋል፤ ሪፖርቶቹን ያጠናቅራል፣ ከተገልጋዮችና ባለድርሻ ምላሽ ይሰጣል፤ ፕሮግራም ያሲዛል፤ ባለጉዳዮችን በቀጠሮ መሠረት ያገናኛል፣ የተቋሙ ኃላፊን የሥራ ቦታ ምቹ በማድረግ ለሥራው መሳካት የሚያግዙ ግብዓቶች እንዲቀርቡና እንዲሟሉ ያደርጋል፣ በሠራተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመመሳከር ያስተናግዳል፣ በተቋሙ ኃላፊ የሚወሰኑ ውሳኔዎች መፈጸማቸውን ይከታተላል፣ የቅሬታና የዱሲፕሊን ኮሚቴዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ እንዲጠናከሩ ያደርጋል፤ የተቋሙ የበላይ ኃላፊ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት የስብሰባውን ፕሮግራምና አጀንዳ ለቢሮ የማኔጅመንት ወይም ለፕሮሰስ ካውንስል አባላትና አስረጂዎች አስቀድሞ ያሳውቃል፣ የማኔጅመንት ወይም የፕሮሰስ ካውንስል ስብሰባዎች ቃላ-ጉባኤ ይይዛል ከቀጣይ ስብሰባ በፊት ቃለ -ጉባኤዎችን በንባብ አቅርቦ ያጸድቃል፤ ያስፈርማል፤ መረጃውን በጥንቃቄ ይይዛል፣ በቃለ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች/ኃላፊዎች በጽሁፍ ያሳውቃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ሪፖርት ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፤

በዘርፉ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች:

ምንም አልተገኘም.